እንኳን ወደ ጉለሌ ፍትህ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!1

ማንኛውንም የክስ ሂደት መከታተያና መረጃ መለዋወጫ ሲስተም

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት

ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች!!

ራዕይ

በ2022 በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የፍትሕ ተቋማት ተምሣሌት ሆኖ ማየት፤

ተልዕኮ

የክ/ከተማ አስተዳደሩንና የነዋሪውን መብትና ጥቅም በማክበርና በማስከበር፣ ንቃተ-ሕግ እንዲዳብር በማድረግ፣ የሕግ ተፈፃሚነትን በማረጋገጥ የላቀ የፍትህ አገልግሎት መስጠት፤

እሴቶች

ግልፅነት፤ ተጠያቂነት፤ ለለውጥ ዝግጁነት፤ አገልጋይነት፤ ፍትሐዊነትና የሕግ የበላይነት፤ ሰብዓዊ ክብር፤ ሙያዊ ብቃት/ፕሮፌሽናሊዝም/፤ ትብብርና አጋርነት፤

የተግባርና ኃላፊነት ትንተና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ እና በተዋረድ የሚገኙ የፍትሕ ተቋማት በአዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 11 ንዑስ-አንቀጽ 9 መሠረት የተቋቋመ ሲሆን በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 25 ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት ውስጥ የክ/ከተማው አስተዳደር ሕጋዊ ወኪል በመሆን በየትኛውም የዳኝነት እርከን በመቅረብ የፍትሕብሔር ክርክር በማድረግ የክ/ከተማ ነዋሪዉንና የአስተዳደሩን መብት እና ጥቅም ማስጠበቅ፤ የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የክ/ከተማዉን የፍትሕ ማሻሻያ ፕሮግራም የታቀዱት ይተገብራል፡፡ ይህን ሲተገብር የሲቪል ማህበረሰብና የነዋሪዉን ተሳትፎ ለማጎልበት የተለያዩ አደረጃጀትና አሰራሮችን ይተገብራል፡፡በአዋጁ ከተሰጡት ዋና ዋና ስልጣንና ተግባራት የነዋሪዉን ንቃተ-ህግ ማሳደግ፣ የተለያዩ አስተዳደሩ የሚያደርጋቸዉን አስተዳደራዊ ዉሎች የማዘጋጀት፣ ረቂቅ ህግ ማዘጋጀት፣ ሰብዓዊ መብትን ከማክበርና ከማስከበር አንፃር የክ/ከተማዉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ በማዘጋጀት መተግበርና በማስተገበር በክ/ከተማዋ የህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በፌደራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣዉን አዋጅ ለማስፈፀም የማስተባበር ሥልጣንና ተግባራትን ያካተተ ነው፡፡

የመረጃ ልውውጥ ሂደቱን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ቀልጣፋ ፍትሃዊና ፈጣን ስራ ለመስራት ወሳኝ ነው፡፡

ወደ ዋናው ፔጅ ለመግባትና ለመመዝገብ